Ethiopian Orthodox Mezmur – Tekle Haimanot – Fantu WoldeEthiopian Orthodox Church, Ethiopian Orthodox Song, Ethiopian Orthodox church, Ethiopian movie, Ethiopian Film, Ethiopian music, Ethiopian Song, Ethiopian Dr…
Watch Ethiopian Mezmur Videos on EthioGospel.com. Share and Like if you like this Mezmur

You might like

8 Comments

 1. Blessed Feast of the Great Saint Tekle Haimanout the Ethiopian Equal of the
  Apostles to all and thank you for uploading this clip 8)

 2. ምንም ሃይማኖቴ ኦርቶዶክስ ባይሆንም እንኩዋን..ዛሬ ዛሬም ከበሮ እና ፅናጸል በሰማሁ ቁጥር 149.99 ጋኔን እና ጂኒ
  ከላየ ላይ እንደ አዋራ ይራገፋል፣ዘውትር ግን ስለኦርቶዶክስ ልቤ በጥያቄ ይሞላል…ለምሳሌ ይቅርታ ይደረግልኝ እና
  አባታችን አቡነ ተክለ ኃይማኖት 7 ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው ጸለዩ etc ይባላል.ከትህትናጋር ነው ምጠይቀው! እስኪ
  አስቡት አንድ እንደ እነ ያሉ ጾመኛ ዕትዩጵያዊ ይቅርና እነ
  Rambo,Bruccly,Chaknoris,Jackichan.አሜርካኖቹ እንድህ አይነት ነገር ይሞክራሉን ? ሮቦት እንኩዋን
  ባትሪ ስያልቅ ይዘለፈለፍ የለምን ? ሌላው በገድላቸዉ ላይ በግልጽ እንደተ ጻፈዉ የሽዋን ህዝብ፣ዋርካ፣አድባር እና ዛፎች
  አስጨፍጭፈዋል ለምን..ከሰላምታ ጋር !

 3. You are not a believer at all! If you believe that God let Paul and peter
  raising a dead and cure chronically ill people, why not believing that he
  gave the ability to do miracles for Ethiopian saints? It is just simple,
  only believe it that’s all! You believed Jesus without seeing him!

 4. አንድ አምላክ፣ በሚሆኑ፣ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ፡ቅዱስ፣ ስም አምኜ ይህችን መልእክቴን ለወንገኔ ወጣቱ ይድረስህ።
  አይ አዲስዘመን100! የተወናያኖቹንም ስም እንኳን በደምብ አላወቅህም እኮ! {“Rambo=Sylvester
  Stallone; Kung fu =Birth name “Lee Jun-fan” Bruce Lee; Chuck Norris; Jackie
  Chan}እነዚህ ለሥራ ተሰማርተው በችሎታቸው እግዚአብሔር በፈቀደላቸው ሙያ እየሰሩ በዓለም ሊታወቁ ቻሉ። በብዙ ድካምና
  ጥናት ያገኙት ውጤት መሆኑን እንዳትዘነጋና እንዳትሳሳት ለማረም ያህል ነው የጻፍኩልህ እንጂ ለሌላ ነገር መስሎህ
  እንዳትጠናወተኝ በቅድሚያ እጠይቃለሁ። እኔ አዋቂ በዕድሜ እንጂ ከአንተ አውቄ አይደለም። ወደ ዋናው ቁም ነገር
  ልመለስና፤ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በገድላቸው ብዙ ተነግሯል። ያንን መጽሐፍ ከቤ/ክ ንዋያተ መደብር ውስጥ በሽያጭ
  መልክ ስለሚገኝ ገዝቶ ማንበቡ ጠቃሚ ይመስለኛል። በዚያውም ለቤ/ክ ድጎማ ይሆናል። መጀመሪያ ሕፃን ሆነህ አባትና እናትህ
  ከርስትና ሳያስነሱህ አይቀርም። የክርስቲያ ቤተሰብ ከሆንክ? ስለዚህ አንድ ጊዜ ተጠምቀሃል ማለት ነው። ለእዚያውም
  ዮሐንስ መጥምቁ መስክሮልናል። ከጊዜ ቆይታ በኋላ ለተከሰቱት ጉዳይ የንስሃ አባት ፈልገህ ለአንድ 3 ወር ያህል ተማር።
  የእዚያን ጊዜ ኹሉም ነገር ይገለጽልሃል። በላይህ ላይ የባሰ ብዙም አቧራ ከአለ በቀላሉ ይራገፋሉ። ልምራህና፦ ማንኛውም
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን በአንድ ሲኖዶስ ስለሚገለገል፤ በዋና መዲናችን በአንድ መንበር የሚተዳደር
  ስለሆነ ስደተኛ የሚባለውም ከእዚያ የወጣም ስለሆነ ቀናውን መንገድ እግዚአብሔር ያሳይህና ወደእዚያ አቅና! ታዳጊ ወጣት
  መኾንህን በአጻጻፍህ ተገንዝቤአለሁ። እኔ እንደ አጋጣሚ ይኸንን አይቼ እንዳላልፍ ብዬ ነው እንጅ፣ ከእኔ የበለጡ እጅግ
  በጣም ብዙ ምኹሮች አሉ። ያስተማርኳቸው ዶክተሮቹ ልጆቼ እንኳን ይበልጡኛል። እኔ በአነጋገርህ አንድ የተሰማኝ ነገር
  አለ። ይኸውም፣ ለማሾፍ የጻፍከው ካልሆነ፡ ምክሬን ተቀበል። በጠቅላላ ያሰፈርኩልህ ፅሑፍ መሬት
  እንዳይወድቁ ተጠቀምበት። የተናገርከውም ስለ ቅዱስ አቡነ ተክለኃይማኖት፣ አሠረ ፍኖት በመቀበል፣ እግዚአብሔር በመራቸው፣
  ዘር ልዝራ ሳይሉ፣ ትዳር ልያዝ ሳይሉ ከአባታቸው ከጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከእግዚእኃረያ በመለየት የክርስቶስን ወንጌል
  በማሰተማርና በማጥመቅ የክርስቶስን መንግሥት እንዲወርሱ ያደረጉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው። ቀደስኩከ እምከርሠ እምከ፣
  ማለት በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፡ ከማሕፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፣ ለአሕዝብ ነቢይ አድርጌሃለሁ፣ እኔም ወዮ ጌታ
  እግዚአብሔር እነሆ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፣ ወደ ምሰድህ ሁሉ
  ዘንድ ትሄዳለህና የማዝዝህን ሁሉ ትናገራለህና ብላቴና ነኝ አትበል እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና ከፊታቸው
  አትፍራ ይላል። ትንቢተ ኤርምያስ ምዕ ፩ ቁጥር ፩ በተባለው መሠረት። በኢትዮጵያ በረሃዎችና አውራጃዎች እየተዘዋወሩ
  በልዩ ልዩ አምልኮት የነበረውብ ሕዝብ የክርስቶስ ወንጌለ መንግሥትን አስተምረውና አጥምቀው የክርስቶስ መንግሥትን
  እንዲወርሱ ያደረጉ ታላቅ ጻድቅ ናቸው። ከእዚህም በላይ ረሃቡንና ጽሙን ታግሠው በጾምና በፀሎት እንዲሁም በስግደት
  ተጋድሎ በማድረግ ለኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን የሠሩት ሥራ ኢትዮጵያ ትኮራባቸዋለች ከእዚህም በላይ በእኒህ ታላቅ ጻድቅ
  ልመናና አማላጅነት ትጠቀማለች። ጌታ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፲ ቁጥር ፵ እንዳለ፣ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣
  እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፣ ነቢዩን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል። ጻድቅንም በጻድቅ ስም
  የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ
  እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ይላል። በእርግጥ ብዙ አሕዛብ ከጣኦት አምልኮ የሚያመልኩበትን ዛፎችና ድንጋዮችን
  በመቆራረጥና በማፈራረስ ወደ ቅዱስ ወንጌለ መንግሥት አምላከ ተክለ ኃይማኖት የኢትዮጵያን ሕዝብ በማዳን መልሰዋል።
  በሉኬ፡ አብሑኒ፡ ፍቁራኒሁ፡ ለአብ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *